(ዋሽንግተን ዲሲ) – ከንቲባ ሙሪኤል ባውዘር የዲስትሪክቱ የአገር ውስጥ ደህንነት እና የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኤጀንሲ (HSEMA) ከዲሲ የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (DHS) ጋር በመተባበር ከዓርብ ህዳር 13 ምሽት 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ህዳር 14 ጠዋት 3:00 ሰዓት ድረስ የብርድ ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ዛሬ አስታውቀዋል። እንደ ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት መረጃ ከሆነ፣ በዋሽንግተን ዲሲ ያለው የምሽቱ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን 37 ዲግሪ ፋራናይት እንደሚሆን እና የንፋሱ ቅዝቃዜ ደግሞ እስከ 32 ዲግሪ ሊደርስ እንደሚችል ይጠበቃል። ነዋሪዎች ንቁ ሆነው እንዲቆዩ እና የመጠለያ የስልክ መስመርን በመደወል መጠለያ የሚያስፈልጋቸውን ቤት አልባ ጎረቤቶችን እንዲረዱ ይበረታታሉ። ለራስዎ ወይም ለሌላ ሰው ነፃ እና ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጠየቅ፣ ወደ መጠለያ የስልክ መስመር (202) 399-7093 ይደውሉ ወይም 311 ላይ ይደውሉ። አስቸኳይ የህክምና ድንገተኛ አደጋ አለ ብለው ካመኑ፣ 911 ይደውሉ። የብርድ ማስጠንቀቂያዎች እና የከባድ ብርድ ማስጠንቀቂያዎች የብርድ ማስጠንቀቂያዎች እና የከባድ ብርድ ማስጠንቀቂያዎች የሚተላለፉት ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት በነዋሪዎች፣ በተለይም ከቤት ውጭ ባሉ እና ቤት በሌላቸው ሰዎች ላይ አደጋ ሊያስከትል የሚችል የአየር ሁኔታ ሲተነብይ ነው። የብርድ ማስጠንቀቂያ የሚተገበረው ከንፋስ ቅዝቃዜ ጋር ያለው የተተነበየው የሙቀት መጠን በሚከተለው መካከል ሲሆን ነው፡ • ከ16° እስከ 32° ፋራናይት፣ ወይም• የዝናብ፣ የበረዶ ወይም የበረዶ ቅንጣት ዝናብ የሚጠበቅ ከሆነ ከ21° እስከ 40°F የነፋስ ቅዝቃዜን ጨምሮ የሚገመተው የሙቀት መጠን ከሚከተሉት በታች ሲወርድ የከባድ ብርድ ማስጠንቀቂያ ይተላለፋል፦ • 15°F፣ ወይም • የዝናብ፣ የበረዶ ወይም የበረዶ ቅንጣት ዝናብ የሚጠበቅ ከሆነ 20°F የብርድ ማስጠንቀቂያዎች እና የከባድ ብርድ ማስጠንቀቂያዎች የዲስትሪክቱ የድንገተኛ አደጋ የህዝብ ማሳወቂያ ስርዓት በሆነው AlertDC በኩል ይጋራሉ። ነዋሪዎች alert.dc.gov ላይ በነጻ የኢሜይል እና የጽሑፍ መልዕክት ማስጠንቀቂያዎችን እና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት መመዝገብ ይችላሉ። የቀዝቃዛ አየር ሁኔታ የደህንነት ጥንቃቄዎች፦ • የሚቻል ከሆነ ቤት ውስጥ ይቆዩ። • ወደ ውጭ በሚወጡበት ጊዜ ሰውነትዎን በደንብ ይሸፍኑ እና ለብርድ የተጋለጠውን የቆዳ ክፍል ይቀንሱ። • ጎረቤቶችዎን ይጠይቁ እንዲሁም በተለይም በህብረተሰባችን ውስጥ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑትን ትንንሽ ልጆች፣ አረጋውያን እና የአካል ጉዳትና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች የሃይፖተርሚያ (የሰውነት ሙቀት ከመጠን በላይ መቀነስ) ምልክቶችን ይወቁ። • ቤት-አልባ ለሆኑ ማናቸውም ሰዎች ሞቅ ያሉ እና አስተማማኝ ቦታዎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ዲስትሪክቱ የሃይፖተርሚያ መጠለያዎችን ይከፍታል። የመጠለያዎችን ዝርዝር እና ስለ ሃይፖተርሚያ ወቅት ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት cold.dc.gov ን ይጎብኙ። • በከባድ ቅዝቃዜ ውስጥ ውጭ የተተዉ እንስሳትን ጨምሮ ለሁሉም የእንስሳት ድንገተኛ አደጋዎች ለBrandywine Valley SPCA በ (202) 888-PETS ይደውሉ። ቀለል ያሉ መስፈርቶች ያሏቸው መጠለያዎች፦የሚከተሉት ዝቅተኛ መስፈርት ያላቸው መጠለያዎች (ከተገለጹት ውጪ) ዓመቱን ሙሉ በሳምንት 7 ቀናት ለ24 ሰዓታት ክፍት ናቸው፦
ሴቶች
• Harriet Tubman – 1910 Massachusetts Avenue SE
• Pat Handy – 810 5th Street NW
• St. Josephine Bakhita – 6010 Georgia Avenue NW (ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ጥዋቱ 1:00 ሰዓት ብቻ)
ወንዶች
• 801 East – 2722 Martin L. King Jr. Avenue SE
• Adams Place – 2210 Adams Place NE
• Emery – 1725 Lincoln Road NE
• New York Avenue – 1355 New York Avenue NE
LGBTQ+
• Living Life Alternatives – 400 50th Street SE
የብርድ ወቅት መጠለያዎች፦
የሚከተሉት የብርድ ወቅት መጠለያዎች አርብ ህዳር 13 አዳር እስከ ቅዳሜ ህዳር 14 ድረስ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ጥዋቱ 3:00 ሰዓት ክፍት ይሆናሉ።
ሴቶች
• Eve’s Place – 2210 Adams Place NE
ወንዶች
• 801 East Day Center – 2722 Martin L. King Jr. Avenue SE
• Emery Hypothermia – 1725 Lincoln Road NE
• Federal City 1 North – 425 2nd Street NW
የብርድ ወቅት መጠለያዎች በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ጥዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ አገልግሎት ይሰጣሉ። አንድ የብርድ ወቅት መጠለያ አንዴ ከተከፈተ በኋላ ወቅቱ እስኪያበቃ ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። የዲስትሪክቱ የመጠለያ ሥርዓት የመያዝ አቅም ገደብ ላይ ከደረሰ ተጨማሪ የብርድ ወቅት መጠለያዎች ይጨመራሉ።እጅግ በጣም የቀዘቀዘ የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ በሚኖርበት ጊዜ፣ የሃይፖተርሚያ መጠለያዎች የስራ ሰዓታቸውን ወደ 24/7 በማራዘም ማስጠንቀቂያው እስኪነሳ ድረስ ሙሉ ቀን እና ለሊት አገልግሎት ይሰጣሉ። እባክዎ ልብ ይበሉ፦ ሁኔታዎች ካስገደዱ (ለምሳሌ፣ የአገልግሎት አቅርቦት ችግሮች፣ ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ የመግቢያ ችግሮች፣ ወዘተ) በስራ ሰዓታት እና በተቋማቱ ላይ ማስተካከያዎች ሊደረጉ ይችላሉ። በሳምንቱ መጨረሻ የአደጋ ጊዜ መጠለያ የሚፈልጉ ቤተሰቦች የመጠለያ የስልክ መስመርን በ(202) 399-7093 ወይም በ311 መደወል ይችላሉ። የከንቲባ ባውዘር X፦ @MayorBowser የከንቲባ ባውዘር ኢንስታግራም፦ @Mayor_Bowser የከንቲባ ባውዘር ብሉስካይ፦ @MayorBowser የከንቲባ ባውዘር ፌስቡክ፦ facebook.com/MayorMurielBowser የከንቲባ ባውዘር ዩቲዩብ፦ የከንቲባ ባውዘር ሊንክድኢን፦ linkedin.
