የኤሌክትሪክ ስኩተሮች (e-scooter) እና የኤሌክትሪክ ብስክሌቶች ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ የሕፃናት ሕይወትና ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ ላይ ወድቋል። በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮፖሊታን (DMV) አካባቢ በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ የ9 ዓመት ልጅ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ እያለ ሕይወቱ ሲያልፍ፣ የ5 ዓመት ልጅ ደግሞ ከባድ ጉዳት የደረሰበት አሳዛኝ