የአሌክሳንድሪያ ከተማ በዱክ ስትሪት ላይ የትራንዚት እና የጉዞ አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያስችሉ የዲዛይን አካላት ላይ ግብአት እየሰበሰበች ነው ለአፋጣኝ መልቀቅ: ጥቅምት 4, 2022 አሁን እስከ ጥቅምት 28 ድረስ ከተማዋ ለዱክ ስትሪት የተቀረጹትን የጎዳና ዲዛይን አካላት ለማጋራት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እና የሚደረጉ ስምምነቶች (tradeoffs) ላይ አስተያየቶችን ለመሰብሰብ የተለያዩ ዝግጅቶችን እና እንቅስቃሴዎችን እያካሄደች ነው፡፡ ይህ የዱክ ስትሪት ኢን ሞሽን ሁለተኛው የማህበረሰብ አስተያየት መሰብሰቢያ ምዕራፍ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በአውቶቡስ ላይ ያተኮረ የማሻሻያ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ከምዕራብ አሌክሳንድሪያ እስከ ኪንግ ስትሪት ሜትሮ ጣቢያ የሚዘረጋ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከሰሜን ቨርጂኒያ የትራንስፖርት ባለስልጣን በሚገኝ 87 ሚሊዮን ዶላር የክልል ገቢ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡ የማህበረሰቡ አስተያየት የትኞቹ አካላት ለተጨማሪ ዲዛይን እና ትንተና እንዲሸጋገሩ ለመወሰን አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
የአሌክሳንድሪያ ከተማ በዱክ ጎዳና ላይ ትራንዚትና ጉዞን ለማሻሻል ስለ የንድፍ አካላት አስተያየት እየጠየቀች ነው።
Local impact analysis
Set your area to see how this story may affect your community.
Related Articles
📰 Source View original ↗
Community Trust CheckDigital Citizen Panel
Rate this article's accuracy and bias. Your feedback directly influences how this story is ranked in the feed.
Are the facts accurate?
Is there a bias?
🤝 Community Notes— auto-translated to your language
Loading...
Add Local Context
🔍 Related Sources & Further Reading
🔍
Finding related sources...