ሜዲኬይድ እና CHIP ሽፋን

  • በሁሉም ግዛቶች ሜዲኬይድ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች፣ ቤተሰቦችን እና ህጻናትን፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችን፣ አረጋውያንን እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ የጤና ሽፋን ይሰጣል።
  • አንዳንድ ግዛቶች የሜዲኬይድ ፕሮግራማቸውን ከተወሰነ የገቢ ደረጃ በታች የሆኑ አዋቂዎችን ለመሸፈን አስፋፍተዋል። ስለ ሜዲኬይድ መስፋፋት እና ለእርስዎ ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ይወቁ።
  • የሜዲኬይድ ፕሮግራሞች የፌዴራል መመሪያዎችን መከተል አለባቸው፣ ነገር ግን ብቁ የገቢ ደረጃዎች፣ ሽፋን እና ወጪዎች ከግዛት ወደ ግዛት ሊለያዩ ይችላሉ።
  • አንዳንድ የሜዲኬይድ ፕሮግራሞች ለህክምናዎ በቀጥታ ይከፍላሉ። ሌሎች ደግሞ የሜዲኬይድ ሽፋን ለመስጠት የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ይጠቀማሉ።
  • ሜዲኬይድ የህክምና አገልግሎት ባገኙበት ወቅት በሜዲኬይድ ባይመዘገቡም እንኳ ላለፉት 3 ወራት የህክምና ወጪዎን ለመክፈል ሊረዳዎ ይችላል። ክፍያው በወቅቱ በቤተሰብዎ ገቢ ላይ የተመሰረተ ነው።
  • የሜዲኬይድ ጥቅሞች በእያንዳንዱ ግዛት ይለያያሉ፣ ነገር ግን ሁሉም ግዛቶች ሁሉን አቀፍ ሽፋን ይሰጣሉ። ሜዲኬይድ በሁሉም ግዛቶች የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ዝርዝር ያግኙ።
  • በተወሰኑ ግዛቶች CHIP ለሜዲኬይድ ብቁ ለመሆን በጣም ብዙ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች ህጻናት እና ነፍሰ ጡር ሴቶች ዝቅተኛ ወጪ የጤና ሽፋን ይሰጣል። CHIP ስለሚሸፍናቸው ነገሮች የበለጠ ይወቁ።
  • እያንዳንዱ ግዛት ከግዛቱ ሜዲኬይድ ፕሮግራም ጋር በቅርበት ይሰራ